ምዕራፍ፡፩።
፩፤ ቶሎ፡ይሆን፡ዘንድ፡የሚገባውን፡ነገር፡
ለባሪያዎቹ፡ያሳይ፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡ለኢ
የሱስ፡ክርስቶስ፡የሰጠው፡በእርሱም፡የትገ
ለጠው፡ይህ፡ነው፥ እየሱስም፡በመልአኩ ፡
፪፤ ልኮ፡ለባሪያው፡ሰዮሐንስ፡አመለከተ፥ እር
ሱም፡ለእግዚአብሔር፡ቃልና፡ለኢየሱስ፡
ክርስቶስ፡ምስክር፡ላየውም ፡ሁሉ፡መሰ
፫፤ ከረ። ዘመኑ፡ቀርቦአልና፡የሚያነበው፥ የትን
ቢቱን፡ቃል፡የሚሰሙትና፡በውስጡ፡የተጻ
ፈውን፡የሚጠብቁት፡ብፁዓን፡ናቸው።
፬፭፤ ዮሐንስ፡በእስያ፡ላሉት፡ለሰባቱ፡አብያተ፡
ክርስቲያናት፤
ካለውና፡ከነበረው፡ከሚመጣውም፥ በዙፋ
ኑም፡ፊት፡ካሉት፡ከሰባቱ፡መናፍስት፡ከታ
መነውም፡ምስክር፡ከሙታንም፡በኩር፡የምድ
ርም፡ነገስታት፡ገዥ፡ከሆነ፡ከኢየሱስ፡ክር
ስቶስ፡ጸጋና፡ሰላም፡ለአናንተ፡ይሁን።
ለወደደን፡ከሃጢአታችንም፡በደሙ፡
፮፤ ላጠበን፥ መንግሥትም፡ለአምላኩና፡ለአባ
ቱም፡ካህናት፡እንድንሆን፡ላደረገ፥ ለእርሱ፡
ከዘላለም፡እስከ፡ዘላለም፡ድረስ፡ክብርና፡
፯፤ ሃይል፡ይሁን፡አሜን። እነሆ፡ከደመና፡
ጋር፡ይመጣል፤ ዓይንም፡ሁሉ፡የወጉትም፡
ያዩታል፥ የምድርም፡ወገኖች፡ሁሉ፡ስለ፡
እርሱ፡ዋይ፡ዋይ፡ይላሉ። አወን፥ አሜን።
፰፤ ያለውና፡የነበረው፡የሚመጣውም፡ሁሉ
ንም፡የሚገዛ፡ጌታ፡አምላክ፦ አልፋና፡
ዖሜጋ፡እኔ፡ነኝ፡ይላል።
፱፤ እኔ ፡ወንድማችሁ፡የሆንሁ፡ከእናንተም፡
ጋር፡አብሬ፡መከራውንና፡መንግስቱን፡የኢ
የሱስ፡ክርስቶስንም፡ትዕግስት፡የምካፈል፡
ዮሐንስ፡ስለ፡እግዚአብሔር፡ቃልና፡ስለ፡
ኢየሱስ፡ምስክር፡ፍጥሞ፡በምትባል፡ደሴት፡
፲፤ ነበርሁ። በጌታ፡ቀን፡በመንፈስ፡ነበርሁ፥
በኋላዬም፡የመለከትን፡ድምፅ፡የሚመስል፡
፲፩ ታላቅ፡ድምፅ፡ሰማሁ፥ እንዲሁም፦ የምታየ
ውን፡በመጽሃፍ፡ጽፈህ፡ወደ፡ኤፌሶንና፡
ወደ፡ሰርምኔስ፡ወደ፡ጴጋርሞንም፡ወደ፡ትያ
ጥሮንም፡ወደ፡ሰርዴስም፡ወደ፡ፊልድልፍ
ያም፡ወደ፡ሎዶቅያም፡በእስያ፡ወዳሉት፡ወደ፡
ሰባቱ፡አብያተ፡ክርስቲያናት፡ላክ፡አለኝ።
፲፪፤ የሚናገረኝንም፡ድምፅ፡ለማየት፡ዘወር፡
አልሁ፤ ዘወርም ፡ብዬ፡ሰባት፡የወርቅ፡መቅ
ረዞች፡አየሁ፥ በመቅረዞቹም፡መካከል፡የሰው፡
ልጅ፡የሚመስለውን፡አየሁ፥ እርሱም፡እስከ፡
እግሩ፡ድረስ፡ልብስ፡የለበሰው፡ደረቱንም፡
፲፬፤ በወርቅ፡መታጠቂያ፡የታጠቀ፡ነበር። ፡ራሱና
የራሱ፡ጠጉርም፡እንደ፡ነጭ፡የበግ፡ጠጉር፡
እንደ፡በረዶም፡ነጭ፡ነበሩ፥ ዓይኖቹም፡እንደ፡
፲፭፤ እሳት፡ነበልባል፡ነበሩ፤ እግሮቹም፡በእቶን፡
የነጠረ፡የጋለ፡ናስ፡ይመስሉ፡ነበር፥ ድምፁም፡
፲፮፤ እንደ፡ብዙ፡ውኃዎች፡ድምፅ፡ነበረ። በቀኝ፡
እጁም፡ሰባት፡ከዋክብት፡ነበሩት፥ ከአፉም፡
በሁለት፡ወገን፡የተሳለ፡ሰለታም፡ሰይፍ፡ወጣ፤
ፊቱም፡በሃይል፡እንደሚበራ፡አንደ፡ፀሐይ፡
ነበረ።
፲፯፤ ባየሁትም፡ጊዜ፡አንደ፡ሞተ፡ሰው፡ሆኜ፡
ከእግሩ፡በታች፡ወደቅሁ። ቀኝ፡እጁንም፡
ጫነብኝ፡እንዲህም፡አለኝ፦ አትፍራ፤ ፊተ
፲፰፤ ኛውና፡መጨረሻው፡ህያውም፡አኔ፡ነኝ፥
ሞቸም፡ነበርሁ፡እነሆም፡ከዘላለም፡አስክ፡
ዘላለም፡ድረስ፡ሕያው፡ነኝ፥ የሞትና፡የሲኦ
፲፱፤ ልም፡መክፈቻ፡አለኝ። እንግዲህ፡ያየኸውን፡
አሁንም፡ያለውን፡ከዚህም፡በኋላ፡ይሆን፡
፳፤ ዘንድ፡ያለውን፡ጻፍ። በቀኝ፡እጄ፡ያየሃቸው፡
የሰባቱ፡ከዋክብትና፡የሰባቱ፡የወርቅ፡መቅ
ረዞች፡ምስጢር፡ይህ፡ነው፤ ሰባቱ፡ከዋክ
ብት፡የሰባቱ፡አብያተ፡ክርስቲያናት፡መላእ
ክት፡ናቸው፥ ሰባቱም፡መቅረዞች፡ሰባቱ፡አብ
ያተ፡ክርስቲያናት፡ናቸው።